የዮሐንስ፡ራእይ።

                ምዕራፍ፡፩። 
፩፤    ቶሎ፡ይሆን፡ዘንድ፡የሚገባውን፡ነገር፡
      ለባሪያዎቹ፡ያሳይ፡ዘንድ፡እግዚአብሔርለኢ
      የሱስ፡ክርስቶስ፡የሰጠው፡በእርሱም፡የትገ
      ለጠው፡ይህ፡ነው፥ እየሱስም፡በመልአኩ ፡
፪፤  ልኮ፡ለባሪያው፡ሰዮሐንስ፡አመለከተ፥ እር
      ሱም፡ለእግዚአብሔር፡ቃልና፡ለኢየሱስ፡
      ክርስቶስ፡ምስክር፡ላየውም ፡ሁሉ፡መሰ
፫፤  ከረ። ዘመኑ፡ቀርቦአልና፡የሚያነበው፥ የትን
      ቢቱን፡ቃል፡የሚሰሙትና፡በውስጡ፡የተጻ
      ፈውን፡የሚጠብቁት፡ብፁዓን፡ናቸው። 
፬፭፤   ዮሐንስ፡በእስያ፡ላሉት፡ለሰባቱ፡አብያተ፡
      ክርስቲያናት፤
        ካለውና፡ከነበረው፡ከሚመጣውም፥ በዙፋ
      ኑም፡ፊት፡ካሉት፡ከሰባቱ፡መናፍስት፡ከታ
      መነውም፡ምስክር፡ከሙታንም፡በኩር፡የምድ
      ርም፡ነገስታት፡ገዥ፡ከሆነ፡ከኢየሱስ፡ክር
      ስቶስ፡ጸጋና፡ሰላም፡ለአናንተ፡ይሁን። 
        ለወደደን፡ከሃጢአታችንም፡በደሙ፡
፮፤  ላጠበን፥ መንግሥትም፡ለአምላኩና፡ለአባ
      ቱም፡ካህናት፡እንድንሆን፡ላደረገ፥ ለእርሱ፡
      ከዘላለም፡እስከ፡ዘላለም፡ድረስ፡ክብርና፡
፯፤  ሃይል፡ይሁን፡አሜን። እነሆ፡ከደመና፡
      ጋር፡ይመጣል፤ ዓይንም፡ሁሉ፡የወጉትም፡
      ያዩታል፥ የምድርም፡ወገኖች፡ሁሉ፡ስለ፡
      እርሱ፡ዋይ፡ዋይ፡ይላሉ። አወን፥ አሜን።
፰፤   ያለውና፡የነበረው፡የሚመጣውም፡ሁሉ
      ንም፡የሚገዛ፡ጌታ፡አምላክ፦ አልፋና፡
      ዖሜጋ፡እኔ፡ነኝ፡ይላል።    
፱፤   እኔ ፡ወንድማችሁ፡የሆንሁ፡ከእናንተም፡
      ጋር፡አብሬ፡መከራውንና፡መንግስቱን፡የኢ
      የሱስ፡ክርስቶስንም፡ትዕግስት፡የምካፈል፡
      ዮሐንስ፡ስለ፡እግዚአብሔር፡ቃልና፡ስለ፡
      ኢየሱስ፡ምስክር፡ፍጥሞ፡በምትባል፡ደሴት፡
፲፤  ነበርሁ። በጌታ፡ቀን፡በመንፈስ፡ነበርሁ፥
      በኋላዬም፡የመለከትን፡ድምፅ፡የሚመስል፡
፲፩  ታላቅ፡ድምፅ፡ሰማሁ፥ እንዲሁም፦ የምታየ
      ውን፡በመጽሃፍ፡ጽፈህ፡ወደ፡ኤፌሶንና፡
      ወደ፡ሰርምኔስ፡ወደ፡ጴጋርሞንም፡ወደ፡ትያ
      ጥሮንም፡ወደ፡ሰርዴስም፡ወደ፡ፊልድልፍ
      ያም፡ወደ፡ሎዶቅያም፡በእስያ፡ወዳሉት፡ወደ፡
      ሰባቱ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ላክ፡አለኝ። 
፲፪፤   የሚናገረኝንም፡ድምፅ፡ለማየት፡ዘወር፡
      አልሁ፤ ዘወርም ፡ብዬ፡ሰባት፡የወርቅ፡መቅ
      ረዞች፡አየሁ፥ በመቅረዞቹም፡መካከል፡የሰው፡
      ልጅ፡የሚመስለውን፡አየሁ፥ እርሱም፡እስከ፡
      እግሩ፡ድረስ፡ልብስ፡የለበሰው፡ደረቱንም፡
፲፬፤  በወርቅ፡መታጠቂያ፡የታጠቀ፡ነበር። ፡ራሱና
      የራሱ፡ጠጉርም፡እንደ፡ነጭ፡የበግ፡ጠጉር፡
      እንደ፡በረዶም፡ነጭ፡ነበሩ፥ ዓይኖቹም፡እንደ፡
፲፭፤  እሳት፡ነበልባል፡ነበሩ፤ እግሮቹም፡በእቶን፡
      የነጠረ፡የጋለ፡ናስ፡ይመስሉ፡ነበር፥ ድምፁም፡
፲፮፤  እንደ፡ብዙ፡ውኃዎች፡ድምፅ፡ነበረ። በቀኝ፡
      እጁም፡ሰባት፡ከዋክብት፡ነበሩት፥ ከአፉም፡
      በሁለት፡ወገን፡የተሳለ፡ሰለታም፡ሰይፍ፡ወጣ፤
      ፊቱም፡በሃይል፡እንደሚበራ፡አንደ፡ፀሐይ፡
      ነበረ። 
፲፯፤   ባየሁትም፡ጊዜ፡አንደ፡ሞተ፡ሰው፡ሆኜ፡
      ከእግሩ፡በታች፡ወደቅሁ። ቀኝ፡እጁንም፡
      ጫነብኝ፡እንዲህም፡አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተ
፲፰፤  ኛውና፡መጨረሻው፡ህያውም፡አኔ፡ነኝ፥
       ሞቸም፡ነበርሁ፡እነሆም፡ከዘላለም፡አስክ፡
       ዘላለም፡ድረስ፡ሕያው፡ነኝ፥ የሞትና፡የሲኦ
፲፱፤  ልም፡መክፈቻ፡አለኝ። እንግዲህ፡ያየኸውን፡
      አሁንም፡ያለውን፡ከዚህም፡በኋላ፡ይሆን፡
፳፤  ዘንድ፡ያለውን፡ጻፍ። በቀኝ፡እጄ፡ያየሃቸው፡
      የሰባቱ፡ከዋክብትና፡የሰባቱ፡የወርቅ፡መቅ
      ረዞች፡ምስጢር፡ይህ፡ነው፤ ሰባቱ፡ከዋክ
      ብት፡የሰባቱ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡መላእ
      ክት፡ናቸው፥ ሰባቱም፡መቅረዞች፡ሰባቱ፡አብ
      ያተ፡ክርስቲያናት፡ናቸው።